• እምነትህ

    እምነትህ

    ወደ ተለያዩ ህዝቦች የተላኩ ነቢያት በሙሉ ይዘው በተነሱት ተልእኮ ውስጥ “አላህ ያለማንም ተጋሪ በብቸኝነት መመለክ ይኖርበታል፡፡ ከርሱ ውጪ ሌላን በማምለክ ሊካድ አይገባውም” የሚል ሙሉ ስምምነት አለ፡፡ ይህ ዕውነታ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” የሚለውን ቃል ያንፀባርቃል፡፡ አንድ ሰው ወደ አላህ ሃይማኖት ሊገባ የሚችለው...

    በተጨማሪ አንብብ
  • ንፅህናህ

    ንፅህናህ

    አላህ (ሱ.ወ) አንድ ሙስሊም ውስጣዊ አካሉን-ልቦናውን ከማጋራትና እንደ ምቀኝነት፣ ኩራትና ተንኮል ካሉ የልብ በሽታዎች፣ውጫዊ አካሉን ደግሞ ከነጃሳና ቆሻሻ ከሆኑ ነገሮች እንዲያፀዳ አዟል፡፡ ይህን ከፈፀመ የአላህን ውዴታ ይጎናጸፋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡-«አላህ (ከኀጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፡፡ ተጥራሪዎችንም ይወዳል፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 222)

    በተጨማሪ አንብብ
  • ሠላትህ

    ሠላትህ

    ሠላት የሃይማኖት መሰረት ነው፡፡ ባሪያውን ከጌታው ጋር የሚያገናኝ መስመር ነው፡፡ ስለሆነም ከአምልኮዎች ሁሉ ታላቁና ደረጃውም እጅግ የላቀ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ አንድ ሙስሊም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እርሷን እንዲጠብቅ አዟል፡፡ ነዋሪም ሆነ መንገደኛ፣ ጤነኛም ሆነ ህመምተኛ፣እንዲተገብራት አዟል፡፡

    በተጨማሪ አንብብ
  • ጾምህ

    ጾምህ

    አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በአመት አንድ ወርን እንዲጾሙ ግዳጅ አድርጎ ደንግጓል፡፡ እሱም የተባረከውን የረመዳንን ወር ነው፡፡ አራተኛ የኢስላም ማዕዘንና ታላቅ መሰረት አድርጎታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ ተፃፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡›› ይላል፡፡ (አል በቀራ 183)

    በተጨማሪ አንብብ
  • ምጽዋትህ (ዘካህ)

    ምጽዋትህ (ዘካህ)

    አላህ (ሱ.ወ) ምጽዋትን ግዴታ አድርጎ ደንግጓል፡፡ ከኢስላም ማዕዘናት መካከል ሦስተኛ አድርጎታል፡፡ እሷን የማይፈፅም ሰውን ብርቱ በሆነ ቅጣት ዝቶበታል፡፡ ኢስላም፣ ንስሃ መግባትን፣ ሠላት ማቋቋምንና ምጽዋት መስጠትን ከሙስሊሞች የወንድማማችነት ትስስር ጋር አቆራኝቶታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ቢፀፀቱም፣ ሠላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ፣ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው...

    በተጨማሪ አንብብ
  • ሐጅህ

    ሐጅህ

    የሐጅ አምልኮን ለመፈፀም ወደ መካ መጓዝ ከኢስላም ማዕዘናት መካከል አምስተኛው ማዕዘን ነው፡፡ ሐጅ፡ በአካል፣ በቀልብና በገንዘብ የሚከናወኑ የአምልኮ ዓይነቶች የሚሰባሰቡበት አምልኮ ዘርፍ ነው፡፡ በአካሉና በገንዘቡ ይህን አምልኮ መፈፀም በቻለ ሰው ላይ ሁሉ በዕድሜው አንድ ጊዜ መፈፀም ግዴታ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ...

    በተጨማሪ አንብብ
  • የንግድ ግንኙነትህ

    የንግድ ግንኙነትህ

    ኢስላም፣ አንድ ግለሰብ ሃብታምም ቢሆን ድሃ፣ ንብረቱን፣ ገንዘቡንና ሞያዊ መብቱን የሚያስከብሩና የሚያስጠብቁ ሕግጋትና ሥርዓቶችን አስቀምጧል፡፡ እንዲሁም ማኅበረሰቡ እርሱ በርሱ በሚተሳሰርበትን፣ ተደጋግፎ የሚያድግበትንና የሚበለጽግበትን የሕይወት ዘርፍን በማመቻቸትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

    በተጨማሪ አንብብ
  • ምግብህና መጠጥህ

    ምግብህና መጠጥህ

    ሐላል ምግብ በኢስላም ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ገንዘብና ቤተሰብ የተባረኩ እንዲሆኑ ሐላል መመገብ የግድ ነው፡፡ ሐላል ምግብ በሚለው ቃል የተፈለገው ትርጓሜ፣ የተፈቀደ፣ በተፈቀደ መንገድ የተዘጋጀ፣ በሌሎች መብት ላይ ድንበር ሳይታለፍ፣ ግፍ ሳይፈፀም የተገኘና በንፁሕ ገንዘብ የተዘጋጀ ምግብ ለማለት ነው፡፡

    በተጨማሪ አንብብ
  • ልብስህ

    ልብስህ

    ልብስ ለሰው ልጅ ከተሰጡ የአላህ ጸጋዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የአደም ልጆች ሆይ ሃፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ፣ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፤ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው ይገሰፁ ዘንድ (አወረደላቸው)፡፡›› (አል አዕራፍ 26)

    በተጨማሪ አንብብ
  • ቤተሰብህ

    ቤተሰብህ

    ኢስላም ቤተሰባዊ ሕይወት እንዲጸናና እንዲረጋ፣ እንዲሁም ቤተሰብን ከሚያበላሹና ከሚያፈርሱ ነገሮች በመጠበቅና በመከላከል ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባጠቃላይ፣ አንድ ቤተሰብ ካማረና ከተስተካከለ የተቀናጀ ግለሰባዊና ማህበረሰባዊ ዋስትናዎችን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

    በተጨማሪ አንብብ
  • ስነ-ምግባርህ በኢስላም

    ስነ-ምግባርህ በኢስላም

    በኢስላም፣ ስነ-ምግባር ማሟያ ወይምትርፍ ነገርአይደለም፤ ይልቁንም፣ በሁሉም ዘርፍ የጠበቀና ጥልቅ ትስስር ያለው የሃማኖት ክፍል ነው፡፡ ስነ ምግባር በኢስላም የላቀና ከፍተኛ ስፍራ አለው፡፡ ይህ ደግሞ በኢስላም ድንጋጌዎችና ህገ ደንቦች ውስጥ በይፋ የሚታይ እውነታ ነው፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩትም መልካም ስነ ምግባሮችን ሊያሟሉ ነው፡፡

    በተጨማሪ አንብብ
  • አዲሱ ሕይወትህ

    አዲሱ ሕይወትህ

    የሰው ልጅ ወደ ኢስላም የገባበት ቅጽበት በሕይወቱ ውስጥ ከባድ ቦታ የሚሰጠው አጋጣሚ ነው፡፡ እውነተኛው ልደቱ ያ ነው፡፡ የመፈጠሩን ሚስጥር የሚረዳው ከዚያ በኋላ ነው፡፡ ገር በሆነው የኢስላም ሕግ መሰረት ሊኖርና ሕያው ሊሆን እንደሚችልም የሚገነዘበው ከዚያች ቅጽበት በኋላ ነው፡፡

    በተጨማሪ አንብብ