አምስቱ የእስልምና መሠረቶች፡-

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ይላሉ «እስልምና በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል፡፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፣ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሰላትን መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ሐጅ ማድረግና ረመዷንን መፆም ናቸው፡፡» (አል-ቡኻሪ፡ 8 ሙስሊም፡16)

እነዚህ አምስቱ መሠረቶች ሃይማኖቱ የተገነባባቸው ዋና ዋና ምሰሶዎች ናቸው፡፡ በሚቀጥሉት ክፍሎች ዝርዝር ሕግና ስርዓታቸውን እናብራራለን፡፡

فأولها الإيمان والتوحيد, وهو الباب القادم بعنوان (إيمانك).

ከዚህ ለጥቆ ደግሞ ሰላት ይከተላል፡፡ ሰላት ከአምልኮዎች (ኢባዳት) ሁሉ የተከበረውና ታላቁ ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡፡ «ሶላት (የሃይማኖቱ) ምሰሶ ነው፡፡» (ቲርሚዚ፥2749)

መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ.) ለማለት የፈለጉት ፥ የእስልምና ሃይማኖት ቀጥ ብሎ ሊቆምና ሊገነባ የሚችለው በሶላት ነው፡፡ ያለ ሶላት ሃይማኖቱን መገንባት አይቻልም ነው፡፡

ሶላት ጤናማና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን መሟላት ካለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ውሰጥ አንዱ ንፅህና (ጠሃራ) ነው፡፡ ስለዚህ «ከእምነትህ» ቀጥሎ «ንፅህናን» ከዚያም «ሶላትህ» ይከተላል፡፡

 አምስቱ የእስልምና መሠረቶች፡-

1   2
ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም መሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር ሶላትን መስገድ
3   4   5
ዘካን መስጠት ረመዷንን መፆም ሐጅ ማድረግ