እስልምና የሚለካው፥ በአንዳንድ ሙስሊሞች ተግባር ሳይሆን በሃይማኖቱ ምንነትና ምንጭ ነው፡፡

ጤናን የሚጎዳ ተግባር የሚፈፅም የጤና ባለሙያ ወይም መልካም ሥነ- ምግባር የሌላው መምህር ቢያጋጥምህ፥ የእነዚህ ሰዎች ተግባር ከተሰማሩበት ሙያ ጋር የማይገጥምና የማይጣጣም በመሆኑ ትገረምና ትደነቅ እንደሆን እንጂ የትምህርትም ሆነ የሕክምና ሙያ ለህብረተሰቡም ሆነ ለብልፅግና የማይጠቅሙ አላስፈላጊ ተግባራት ናቸው ወደሚል ድምዳሜ አትደርስም፡፡

ባይሆን ልትል የምትችለው ይህ ሐኪምም ሆነ መምህር ከተሰማራበት ሙያ ጋር የማይጣጣም ተግባር እየከናወነ ነው፡፡

አንዳንድ ሙስሊም ግለሰቦች ተገቢ ያልሆነ ተግባር ሲፈፅሙ ካየን፥ ተግባራቸው እስልምናን እያንፀባረቀ እንደሆነ አድርገን መቁጠር አይኖርብንም፡፡ ይልቁንም ልክ ሐኪሙና መምህሩ ከሙያቸው ጋር የሚቃረን ተግባር በልምድ እንዳከናወኑት ሁሉ፥ ከእስልምና ጋር በጭራሽ ግንኙነት የሌለው በልምድና በባህል እንዲሁም በሰብዓዊው ፍጡር ድክመት የሚሰሩ መጥፎ ተግባራት መሆናቸውን ማወቅ አለብን፡፡