ልብስህ

ልብስ ለሰው ልጅ ከተሰጡ የአላህ ጸጋዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የአደም ልጆች ሆይ ሃፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ፣ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፤ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው ይገሰፁ ዘንድ (አወረደላቸው)፡፡›› (አል አዕራፍ 26)