ሐጅህ

የሐጅ አምልኮን ለመፈፀም ወደ መካ መጓዝ ከኢስላም ማዕዘናት መካከል አምስተኛው ማዕዘን ነው፡፡ ሐጅ፡ በአካል፣ በቀልብና በገንዘብ የሚከናወኑ የአምልኮ ዓይነቶች የሚሰባሰቡበት አምልኮ ዘርፍ ነው፡፡ በአካሉና በገንዘቡ ይህን አምልኮ መፈፀም በቻለ ሰው ላይ ሁሉ በዕድሜው አንድ ጊዜ መፈፀም ግዴታ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡›› (አለ ዒምራን 97)