ሠላትህ

ሠላት የሃይማኖት መሰረት ነው፡፡ ባሪያውን ከጌታው ጋር የሚያገናኝ መስመር ነው፡፡ ስለሆነም ከአምልኮዎች ሁሉ ታላቁና ደረጃውም እጅግ የላቀ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ አንድ ሙስሊም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እርሷን እንዲጠብቅ አዟል፡፡ ነዋሪም ሆነ መንገደኛ፣ ጤነኛም ሆነ ህመምተኛ፣እንዲተገብራት አዟል፡፡