-
እምነትህ
እምነትህ
ወደ ተለያዩ ህዝቦች የተላኩ ነቢያት በሙሉ ይዘው በተነሱት ተልእኮ ውስጥ “አላህ ያለማንም ተጋሪ በብቸኝነት መመለክ ይኖርበታል፡፡ ከርሱ ውጪ ሌላን በማምለክ ሊካድ አይገባውም” የሚል ሙሉ ስምምነት አለ፡፡ ይህ ዕውነታ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” የሚለውን ቃል ያንፀባርቃል፡፡ አንድ ሰው ወደ አላህ ሃይማኖት ሊገባ የሚችለው...
በተጨማሪ አንብብ -
ንፅህናህ
ንፅህናህ
አላህ (ሱ.ወ) አንድ ሙስሊም ውስጣዊ አካሉን-ልቦናውን ከማጋራትና እንደ ምቀኝነት፣ ኩራትና ተንኮል ካሉ የልብ በሽታዎች፣ውጫዊ አካሉን ደግሞ ከነጃሳና ቆሻሻ ከሆኑ ነገሮች እንዲያፀዳ አዟል፡፡ ይህን ከፈፀመ የአላህን ውዴታ ይጎናጸፋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡-«አላህ (ከኀጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፡፡ ተጥራሪዎችንም ይወዳል፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 222)
በተጨማሪ አንብብ -
ሠላትህ
ሠላትህ
ሠላት የሃይማኖት መሰረት ነው፡፡ ባሪያውን ከጌታው ጋር የሚያገናኝ መስመር ነው፡፡ ስለሆነም ከአምልኮዎች ሁሉ ታላቁና ደረጃውም እጅግ የላቀ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ አንድ ሙስሊም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እርሷን እንዲጠብቅ አዟል፡፡ ነዋሪም ሆነ መንገደኛ፣ ጤነኛም ሆነ ህመምተኛ፣እንዲተገብራት አዟል፡፡
በተጨማሪ አንብብ -
ጾምህ
ጾምህ
አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በአመት አንድ ወርን እንዲጾሙ ግዳጅ አድርጎ ደንግጓል፡፡ እሱም የተባረከውን የረመዳንን ወር ነው፡፡ አራተኛ የኢስላም ማዕዘንና ታላቅ መሰረት አድርጎታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ ተፃፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡›› ይላል፡፡ (አል በቀራ 183)
በተጨማሪ አንብብ