የሃይማኖቱን ሕግጋት እንዴት አውቃለሁ?

አንድ ሰው ህመም ካጋጠመውና ይህን ህመሙን የሚያሽር መፍትሄ ከፈለገ፥ በዘርፉ ብቃት ያላቸው የህክምና ባለሞያዎች ማፈላለጉ የማይቀር ነው፡፡ ህይወቱ እጅግ ውድ ዋጋ ያላት በመሆኗ ሐኪሙ ያዘዘለትን መድሃኒት በታዘዘው መሠረት በአገባቡ ከመውሰድ እንደማይዘናጋ እሙን ነው፡፡

ሃይማኖት ደግሞ ለሰው ከምንም በላይ ውድ ነገር ነው፡፡ ሃይማኖቱን ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ የማያውቀውን ነገር ለመረዳትም ታማኝ የሆኑ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቆ መረዳት ይኖርበታል፡፡

ይህን መፅሐፍ ማንበብህ ስለ ሃይማኖትህ በትክክል በማወቁ ረገድ እርምጃዎችን እንድትጀምር ያደርግሃል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል«…የማታውቁ ብትሆኑ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ፡፡» (አል-ነሕል፡43) ይህን መጽሐፍ ከማንበብ ባሻገርም ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድም ይኖርብሃል፡፡ አንዳንድ ከበድ ያሉ ሁኔታዎች ሲገጥሙህ በአካባቢህ ያሉ መሳጂዶችና ኢስላማዊ ማዕከሎች ጎራ በማለት ጠይቀህ መረዳት ይኖርብሃል፡፡ ተከታዩን ድረ-ገፅ በመጎብኘትም መረጃዎችን ማግኘት ትችላለህ፡፡ www.islamicfinder.org

የእስልምና ሃይማኖት ዕውታዎችን በማብራራቱ ረገድ ታማኝ የሆነውን ተጨማሪ ድረ-ገፅ መጎብኘትም ይኖርብሃል፡፡

newmuslimguide.com

www.guide-muslim.com