ጾምህ

አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በአመት አንድ ወርን እንዲጾሙ ግዳጅ አድርጎ ደንግጓል፡፡ እሱም የተባረከውን የረመዳንን ወር ነው፡፡ አራተኛ የኢስላም ማዕዘንና ታላቅ መሰረት አድርጎታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ ተፃፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡›› ይላል፡፡ (አል በቀራ 183)