ምግብህና መጠጥህ

ሐላል ምግብ በኢስላም ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ገንዘብና ቤተሰብ የተባረኩ እንዲሆኑ ሐላል መመገብ የግድ ነው፡፡ ሐላል ምግብ በሚለው ቃል የተፈለገው ትርጓሜ፣ የተፈቀደ፣ በተፈቀደ መንገድ የተዘጋጀ፣ በሌሎች መብት ላይ ድንበር ሳይታለፍ፣ ግፍ ሳይፈፀም የተገኘና በንፁሕ ገንዘብ የተዘጋጀ ምግብ ለማለት ነው፡፡