አካባቢህና ቤተሰብህ

አንድ አዲስ ሙስሊም ወደ ኢስላም ከገባበት ጊዜ አንስቶ ከሚያውቃቸው ሰዎች እንዲሁም ከሙስሊም ወይም ሙስሊም ካልሆኑ ዘመዶቹ ጋር ያለውን ግንኙነትና ቅርርብ ይበልጥ ማጠናከር አለበት፡፡ ኢስላም እራስን ወደ ማግለልና ወደ ባይተዋርነት የሚጣራ ሃይማኖት አይደለም፡፡

ለሰዎች በጎ መዋልና ከነርሱ ጋር በመልካም ስነ ምግባር መኗኗር፣ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) መልካም ስነ ምግባሮችን ለማሟላት የተላኩበት የሆነውን ሃይማኖት ለሌሎች ከሚያስተዋውቁ መንገዶች ሁሉ በላጩና ውጤታማው ነው፡፡

የላቁ ስነ ምግባሮች በተግባር የሚተረጎምባቸውና የተከበሩ መልካም ግንኙነቶች የሚንጸባረቅባቸው እርምጃዎች የመጀመሪያው ከቤተሰብ ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡ (ገጽ፣ 213 ተመልከት)

የሚከተሉት መርሆች አንድ አዲስ ሙስሊም ከቤተሰቡ ጋር በሚኖረው ትስስር ሊያውቃቸው የሚገቡ ናቸው፡

 ወደ ኢስላም ከተገባ በኋላ ያለው ቤተሰባዊ ሕይወት

ባልና ሚስት በአንድነት ከሰለሙ

ባልና ሚስት አብረው ከሰለሙ የነበራቸው የጋብቻ ውል ወይም ኒካሕ በኢስላምም ይጸናል፤ የጋብቻውን ውል እንደ አዲስ ማደስ አያስፈልጋቸውም፡፡

ግን ይህ የማያካትታቸው ተንጠለው የሚወጡ ሁኔታዎች አሉ፡

  1. ጋብቻውን የፈፀመው በሸሪዓው ማግባት ከማይፈቀድለት(መሓሪሞች) መካከል ከአንዷ ጋር ከሆነ፡ ለምሳሌ ከእናቱ ወይም ከእህቱ ወይም ከአክስቱ ጋር ጋብቻ ፈፅሞ የነበረ ከሆነ፣ ከሰለሙ ጊዜ ጀምሮ እንዲፋቱ ማድረግ የግድ ነው፡፡ (ገጽ፣ 200 ተመልከት)
  2. ሁለት እህትማማቾችን ወይም ሴቷን ከአክስቷ ጋር ወይም ሴቷን ከየሹሜዋ ጋር በአንድነት አግብቶ ከሆነም አንዳቸውን የመፍታት ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  3. እሱና ሚስቶቹ በአንድ ላይ ቢሰልሙና የሚስቶቹ ብዛት ከአራት በላይ ቢሆን፣ ከአራት ሴቶች በላይ ስለማይፈቀድለት ከነርሱ መካከል አራቱን መርጦ በማስቀረት የተቀረቱን ይፈታቸዋል፡፡

እርሱ ሰልሞ ሚስቱ ባትሰልም የሚኖረው ድንጋጌስ ምንድነው?

በዚህ ጊዜ የሴቷ ሃይማኖት ግምት ውስጥ ይገባል፤ የመጽሐፍት ባለቤት፣ ማለትም አይሁድ ወይም ክርስቲያን ልትሆን ትችላለች፤ አለያም እንደ ቡድሂዝም ሂንዱዊዝምና ጣዖት አምላኪያን መጽሐፍት የለሽ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ልትሆን ትችላለች፤ ወይም በሃይማኖት የማታምን ሃይማኖት አልባ ልትሆንም ትችላለች፡፡ እና ፍርዱ ምንድን ነው?

  1. የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ የሆነች ሚስት

አንድ ሰው ቢስልምና ሚስቱ ግን ባትሰልም፣ የመጽሀፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ ብትሆን፣ የጋብቻው ውል በነበረበት ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሙስሊም አንዲትን የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ ሴትን ቢያገባ አይከለከልም፡፡ ስለሆነም ይህም የሰለመ ሰው ከሚስቱ ጋር የጋብቻ ሕይወቱን መቀጠሉና በሚስትነት እሷን ይዞ መቆየቱ የተሻለ ነው፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ዛሬም መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፤ የነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለናንተ የተፈቀደ ነው፤ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፤ ከምእመናት ጥብቆቹም ከነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፉን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፡፡›› (አል ማኢዳ 5)

ነገር ግን ባገኘው አጋጣሚና ብልሃት በመጠቀም እሷን ወደ እስልምና በመጥራቱ ላይ ከፍተኛ ጥረት ሊያደርግ ይገባል፡፡

  1. የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ ያልሆነች ሚስት

ሰውየው ሰልሞ ሚስቱ ኢስላምን ለመቀበል ባትሆንና በሃይማኖቷ የመጽሐፍቱ ባለቤት ተከታይ -አይሁድ ወይም ክርስቲያን- ባትሆንና ቡድሂስት ወይም ሂንዱዊስት ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም የሌላ እምነት ተከታይ ከሆነች፡-

አንዲት ፍች ሴት የምትጠብቀውን ወቅት ያክል ይጠብቃል፡፡ ዝርዝሩ ከዚህ ቀጥሎ ባለው ክፍል ሰንጠረዥ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡

  • በዚህ ቆይታ ውስጥ ከሰለመች ሚስትነቷ ይቀጥላል፡፡ የጋብቻውን ውል በአዲስ መልክ መፈፀም አያስፈልግም፡፡
  • ወቅቱ እስከሚያልቅ ድረስ ተጠብቃም ኢስላምን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነች ግን ጋብቻው ይፈርሳል፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላ ከሰለመችና ሊያገባት ከፈለገ እንደ አዲስ ለጋብቻ ያጫትና ያገባታል፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የከሃዲዎቹንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ፡፡›› (አል ሙምተሒናህ 10) ከሰለማችሁ በኋላ ከመጽሐፍት ባለቤት ሌላ የካሃዲያንን ሴቶች በጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ ማለት ነው፡፡

የተፈታች ሴት ዒዳ (ፍች የሚፀናበት ጊዜ)
  የጋብቻ ውል ፈፅሞ፣ ይዟት ያልገባት- ግብረ ስጋ ግንኙነት አብሯት ያልፈፀመ- ወይም አብሯት ኑሮ ያልጀመረ ሰው ከፈታት፣ ፍቺውን በመፈፀሙ ብቻ ከርሱ ትለያለች፡፡ በያዝነው ርዕስ መሰረት ደግሞ እሱ ብቻውን በመስለሙ ብቻ ከርሱ ትለያለች፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ ምእመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኩዋቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በነሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡›› (አል አህዛብ 49)
  የእርጉዝ ሴት ዒዳ፣ ያረገዘችውን በመውለዷ ያበቃል፡፡ ጊዜው ቢረዝምም ቢያጥርም ልዩነት የለውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡›› (አል ጠላቅ 4)
  እርጉዝ ያልሆነችና የወር አበባ የምታይ ሴት ዒዳዋ ከተፈታች በኋላ ወይም ባል ከሰለመ በኋላ ሦስት ሙሉ የወር አበባ ማየት ነው፡፡ የወር አበባ ደም መጥቶባት ትጸዳለች፤ ከዚያም በድጋሚ ይመጣባትና ትጸዳለች፤ ከዚያም ለሦስተኛ ጊዜ ይመጣባትና ትጸዳለች፤ ሦስት ሙሉእ የወር አበባ ጊዜ የሚባለው ይህ ነው ፡፡ በወር አበባዎቹ መሐከል ያለው ጊዜ ቢረዝምም ባይረዝምም ልዩነት አይኖረውም፡፡ ይህች ሴት ከሦስተኛው የወር አበባ መጽዳት በኋላ ከታጠበች ዒዳዋ ያበቃል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹የተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁሩእ (ሦስትን አደፍ ወይም ሦስትን የአደፍ ጥራት) ይጠብቁ፡፡›› (አል በቀራ 228)
  ያልደረሰች ሕፃን በመሆኗ፣ ወይም ዕድሜዋ በመግፋቱ፣ ወይም ባለባት ዘውታሪ በሽታ ምክንያት የወር አበባ የማታይ ሴት፣ ከተፈታችበት ጊዜ፣ ወይም ባሏ ከሰለመበት ጊዜ አንስቶ ሦስት ወራቶችን ትጠብቃለች፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከሴቶቻችሁ ከአደፍ ያቋረጡት (በዒዳቸውሕህግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፤ እኒያም ገና አደፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡)›› (አል ጠላቅ 4)

ሚስት ካልሰለመች

የመጽሐፍት ባለቤት -አይሁድ ወይም ክርስቲያን- ነች?
አዎን
ጋብቻው በነበረበት ይቀጥላል፤ ማደስ አይፈልግም፤ ወንድየው ለሚስቱ ተስማሚ በሆኑ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም ጥሪ ሊያደርግላት ይገባል፡፡
አይቻልም(በፍፁም)
አይደለችም፡ የመጽሀፍት ባለቤት ካልሆነች በመጀመሪያ ወደ ኢስላም ጥሪ ያደርግላታል፤ ከዚያም በዒዳ ወቅት ኢስላምን ተቀብላለች ወይስ አልተቀበለችም ማለትን እናያለን፡፡
አዎን
እሷ በኢስላም ውስጥም ሕጋዊ ባለቤቱ ናት የጋብቻቸውን ውል ማደስ አያስፈልግም፡፡
አይቻልም(በፍፁም)
የዒዳዋ ወቅት እስከሚያበቃ ድረስ ኢስላምን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነች፣ የጋብቻው ውል ይፈርሳል፤ በሰለመች ጊዜ በአዲስ የጋብቻ ውል ሊጋቡ ወይም ሊማለሱ ይችላሉ፡፡

ሴቷ ሰልማ ባሏ ባይሰልም ፍርዱ ምንድን ነው?

ሁለት ባልና ሚስቶች አብረው ከሰለሙ፣ እንደ ወንድምና አጎት በኢስላም ሊጋቡ የማይፈቀድላቸው ካልሆኑ በስተቀር የጋብቻቸው ውል ባለበት ይጸናል፡፡ (ገጽ፣ 199 ተመልከት)

ሴቷ ሰልማ ባልየው ኢስላምን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፣

በመስለሟ ብቻ የጋብቻው ውል ወደ ምርጫ ይቀየራል፤ ማለት ሚስት የመምረጥ መብት ይሰጣታል፡፡

  • የባሏን መስለም በትዕግስት መጠበቅ፡፡ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለባለቤቷ የኢስላምን እውነታ ማብራራትና መግለጽ አለባት፡፡ አላህ ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዲመራው መማጸን ይኖርባታል፡፡ ከረዥም ጊዜ በኋላ ቢሆንም በዚህ ጥረቷ ከሰለመ መስለሙን እየተጠባበቀች እስከሆነ ድረስ በመጀመሪያው የጋብቻ ውል መሰረት በሚስትነቷ ከሱ ጋር መኖር ትጀምራለች፡፡ ከመስለሙ በፊት ግን ከእሷ ጋር እንዲተኛ ልትመቻችለት ወይም ልትፈቅድለት አይገባትም፡፡
  • ይሰልማል የሚል ተስፋ የማይጣልበት ነው በምትልበት ጊዜ ፍቺ የመጠየቅና የጋብቻውን ውል የማፍረስ መብት አላት፡፡

ከሰለመች ጊዜ አንስቶ በሁለቱም ሁኔታዎች ለካሃዲ ባሏ እራሷን ለግንኙነት ማመቻቸት አይፈቀድላትም፡፡ እራሷን ማመቻቸቷ እርም ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹አማኞችም መኾናቸውን ብታውቁ ወደ ከሃዲዎቹ አትመልሱዋቸው እነርሱ (ሴቶቹ) ለነርሱ የተፈቀዱ አይደሉም፤ እነርሱም (ወንዶቹ) ለነርሱ አይፈቀዱምና፡፡›› (አል ሙምተሒና 10)

በዚህ መመሪያ መሰረት አንዲት ሴት ከሰለመችበት ጊዜ አንስቶ የሚከተለውን መፈፀም ይኖርባታል፡

  1. ከሰለመችበት ጊዜ አንስቶ የምታገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅማ በብልሃትና በመልካም ተግሳጽ ባሏን ወደ ኢስላም መጥራት አለባት፡፡
  2. ባል ኢስላምን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፣ እርሱን ለማሳመን ካልቻለች፣ ካልተሳካላት፣ ወይም በርካታ ሙከራዎችን አድርጋ ተስፋ የመቁረጥ ደረጃ ላይ ከደረሰች፤ በፍጥነት ከርሱ ጋር የምትፋታበትንና የምትለያይበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርባታል፡፡
  3. ለመፈታትና ከሱ ጋር ለመለያየት የሚወስድባት ጊዜ የሚረዝም ከሆነ በመካከላቸው ያለው የጋብቻ ውል ሕጋዊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ባል በዚህ መሐከል ከሰለመ የዒዳ ወቅት ቢጠናቀቅም በመጀመሪያው የጋብቻ ውል ትዳራቸው መቀጠል ይችላል፡፡ አስፈላጊው ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ ባል ካልሰለመና ዒዳው ካለቀ ግን የጋብቻው ውል ይፈርሳል፡፡
  4. የፍቺው ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ ሚስት ትዳር በመሰረተችበት ቤት ውስጥ መቆየት ትችላለች፤ ይሁን እንጂ ከሰለመችበት ጊዜ ጀምሮ ባለው ቆይታ ውስጥ ለግብረ ስጋ ግንኙነት እራሷን ለባሏ ማመቻቸት አይፈቀድላትም፤ እርም ነው፡፡

የሕፃናት መስለም

ሰዎች በሙሉ የሚወለዱት በተፈጥሯዊው እምነት በኢስላም ላይ ነው፡፡ ሌሎች ሃይማኖቶች ወላጆቻቸው በሚያስተምሯቸው ትምህርት ምክንያት በደባልነት የሚገቡባቸው ናቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ልጅ ሁሉ የሚወለደው በተፈጥሯዊ እምነት- በኢስላም- ላይ ነው፡፡ ወላጆቹ ግን አይሁድ ወይም ክርስቲያን ወይም እሳት አምላኪ ያደርጉታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1292 / ሙስሊም 2658)

ከካሃዲያን ቤተሰብ ተወልደው በሕፃንነታቸው የሞቱ ልጆች፣ በዚህ ዓለም ከነሱ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ልክ ከካሃዲያን ጋር የምናደርገው ዓይነት ነው፡፡ አላህ ሚስጥርንና ከዚያም በላይ የተደበቀን ነገር ዓዋቂ ነው፤ እርሱ ዘንድ አንድም ሰው አይበደለም፡፡ እነኚህ ልጆች በትንሳኤው ቀን ፈተና ያቀርብላቸዋል፤ ይፈተናሉ፤ በዚያ ፈተና ታዛዥ የሆነ ጀነት ይገባል፤ አመጸኛ የሆነ ደግሞ እሳት ይገባል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ አጋሪያን ልጆች በተጠየቁ ጊዜ፡- ‹‹አላህ ገና ሲፈጥራቸው ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ ያውቃል፡፡›› በማለት መልሰዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 1317)

በዱንያ ላይ የካሃዲያን ልጆች ሰልመዋል የምንለው መች ነው?

የሕፃናትን መስለም ለማጽደቅ የተለያዩ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡ እነሱም፡

  1. ወላጆች ከሰለሙ፤ ወይም አንዳቸው ከሰለመ፤ ልጅ ከወላጆቹ መካከል በሃይማኖት የተሻለ የሆነውን ይከተላል፡፡
  2. ለሃላፊነት ያልበቃ ወይም ያልጎረመሰ፣ ነገር ግን ክፉና ደጉን የለየ ታዳጊ ሕፃን ከሰለመና ወላጆቹ ካልሰለሙስ? አንድ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሲያገለግል የነበረ አይሁድ ታዳጊ ልጅ ከዕለታት አንድ ቀን ታሞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሊጠይቁት መጡና ከራሱ አጠገብ ቁጭ ብለው ‹‹ስለም›› አሉት፤ የልጁ አባት አጠገቡ ነበርና ልጁ ወደ አባቱ ተመለከተ፤ አባቱም «የቃሲምን አባት ታዘዛቸው» አለው፤ ልጁም ሰለመ ከዚያን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከልጁ ዘንድ ሲወጡ፣ ‹‹ይህን ልጅ ከእሳት ነፃ ያወጣው አላህ የተመሰገነ ይሁን›› አሉ፡፡ (አል ቡኻሪ 1290)
ወላጆቹ በአንድነት ነው የሰለሙት ወይስ አንዳቸው ብቻ ነው የሰለመው?
አዎን
አንድ ላይ ነው የሰለሙት፡ እስልምናው ይጸድቃል፤ በሙስሊሞች ሕግና ደንብ መሰረት ይኗኗራል፡፡
አይቻልም(በፍፁም)
ከቤተሰቡ ተነጥሎ ለብቻው ነው የሰለመው?
አዎን
አዎ፡ የሚናገረውን የሚገነዘብና ክፉና ደጉን የሚለይ ከሆነ በዱንያ ላይ መስለሙ ይጸድቅለታል፡፡ ይህ የኢስላም ሊቃውንት ስምምነት ነው፡፡ በአኼራም ይጠቅመዋል፤ ያድነዋል፤ በሚል ሙስሊሞች በሙሉ በአንድ ድምፅ አጽድቀውታል፡፡
አይቻልም(በፍፁም)
የከሃዲያን ልጆች ሲሞቱ፣ እነሱን በተመለከተ በዱንያ ላይ ያለው ግንኙነታችን የሚከናወነው ከከሃዲያን እንዳለን ግንኙነት ዓይነት ነው፡፡ አላህ ሚስጥርና ከርሱም በላይ የተደበቀን ነገር ዐዋቂ ነው፤ ‹‹ጌታህ አንድንም ሰው አይበድልም››፤ እናም የትንሳኤ ቀን ይፈትናቸዋል፤ በፈተናው ለርሱ ታዛዥ የሆነ ወደ ጀነት ይገባል፤ ያመፀ ደግሞ ወደ እሳት ይገባል፡፡