የምሰግደው እንዴት ነው? ( ቂያም፤ ሩኩዕ፤ ሱጁድ)
-
ቀጥ ብሎ በመቆም እጆቹን በትከሻውና በጆሮው መካከል ከፍ በማድረግ ‹‹አላሁ አክበር›› ይላል፡፡
-
ቀኝ እጁን በግራ እጁ ላይ ደርቦ በማጣመር ደረቱ ላይ ያደርጋል፤ የፋቲሓን ምዕራፍና ከቁርኣን የገራለትን አንቀጽ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ረከዓ ላይ ያነባል፡፡
-
ከዚያም እጆቹን ከፍ በማድረግ ‹‹አላሁ አክበር›› ይላል፤ በቂብላ አቅጣጫ ከወገቡ ጎንበስ በማለት ጉልበቱን በእጁ በመያዝ ሦስት ጊዜ ደጋግሞ ‹‹ሱብሐነ ረቢየል ዐዚም›› ይላል፡፡
-
ከሩኩዕ ቀና በማለት ቀጥ ብሎ ይቆማል፤ በዚህን ጊዜ እጁን በተክቢራ ላይ እንደሚያደርገው ከፍ ያደርጋል፤ ኢማም ሆኖ ወይም ብቻውን የሚሰግድ ሰው ከሆነ ደግሞ ‹‹ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደሁ›› ይላል፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም ‹‹ረበና ወለከል ሐምድ›› ይላሉ፡፡
-
‹‹አላሁ አክበር›› እያለ ወደ ሱጁድ ይወርዳል፤ እጁን ግን ከፍ አያደርግም፤ ሱጁድ የሚያደርገው በሰባት የሰውነት ክፍሎቹ ነው፤ እነርሱም፡ ግንባሩና አፍንጫው፤ እጆቹ፤ ጉልበቶቹና እግሮቹ ናቸው፤ በሱጁድ ላይ ሆኖ ሦስት ጊዜ ‹‹ሱብሐነ ረቢየል ዐዚም›› ይላል፡፡
-
ከሱጁድ ቀና በማለት ወደ ሁለተኛ ረከዓ ይቆማል፤ ከዚያም በመጀመሪያ ረከዓ ላይ ያከናወነውን ደግሞ ያከናውናል፤ ይኸውም መቆም፤ ቁርኣን ማንበብ፤ ሩኩዕ ማድረግ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለትና ሱጁድ ማድረግ ነው፡፡
-
የሚሰግደው ሠላት ባለ ሦስት ወይም ባለ አራት ረከዓዎች ከሆነ ወደ ሦስተኛ ረከዓ ይቆማል፤ ከዚያም በመጀመሪያውና በሁለተኛው ረከዓ ላይ የሰራቸውን ስራዎች በሙሉ ደግሞ ይሰራል፡፡ ግን ከፋቲሓ በኋላ ሌላ ምዕራፍ አያነብም፡፡ የተቀሩት ስራዎችና ንግግሮች ካለፉት ረከዓዎች ጋር አንድ ዓይነቶች ናቸው፡፡
-
በመጨረሻው ረከዓ ከሱጁድ በኋላ ቁጭ ብሎ የመጀመሪያውን ተሸሁድ ይላል፤ በተጨማሪም በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሠለዋት ያወርዳል፤ አባባሉም በሚከተለው መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡ ‹‹አላሁምመ ሠሊ ዐላ ሙሐመድ ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ሠልለይተ ዓላ ኢብራሂመ ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፤ ወባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ባረክተ ዓላ ኢብራሂም ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡››
-
ከዚያም ‹‹አሰላሙዐለይኩም ወረሕመቱላህ›› በማለት ወደ አንገቱን ቀኝ አቅጣጫ ያዞራል፤ ከዚያም ወደ ግራውም በመዞር ‹‹አሰላሙዐለይኩም ወራሕመቱላህ›› ይላል፡፡ በዚህ መልክ ሠላቱን ያጠናቅቃል፡፡