ውዱእ የማደርገው እንዴት ነው?

ውዱእና ከቆሻሻ መጸዳዳት፣ ትሩፋት የሚያስገኙና የላቁ ተግባራት ናቸው፡፡ አንድ ባሪያ ዓላማውን ካሳመረና ለአላህ ካጠራ፣ እንዲሁም ከአላህ ምንዳን ከከጀለበት፣ አላህ በርሱ ወንጀሉንና ስህተቱን ያብስለታል፡፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)፡-«አንድ ሙስሊም ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ፡ ፊቱን ሲታጠብ፣ በዓይኑ በመመልከት የሰራው የእይታ ወንጀል ከውሃው ጋር ከፊቱ ይወገዳል፡፡ እጁን ሲታጠብ፣ በእጁ የፈፀመው ወንጀል ከውሃው ጋር ይወገዳል፡፡ እግሮቹን ሲያጥብ፣ በእግሮቹ በመጓዝ የፈፀመው ወንጀል ከውሃው ጋር ከእግሮቹ ይወገዳል፡፡ በዚህ መልኩ ከወንጀል ጽዱዕ ሆኖ ይወጣል፡፡» ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 244)