ምጽዋትህ (ዘካህ)
አላህ (ሱ.ወ) ምጽዋትን ግዴታ አድርጎ ደንግጓል፡፡ ከኢስላም ማዕዘናት መካከል ሦስተኛ አድርጎታል፡፡ እሷን የማይፈፅም ሰውን ብርቱ በሆነ ቅጣት ዝቶበታል፡፡ ኢስላም፣ ንስሃ መግባትን፣ ሠላት ማቋቋምንና ምጽዋት መስጠትን ከሙስሊሞች የወንድማማችነት ትስስር ጋር አቆራኝቶታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ቢፀፀቱም፣ ሠላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ፣ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡›› (አል ተውባ 11) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹ኢስላም በአምስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ተገነባ፡፡›› ‹‹…..ሠላትን ማቋቋም፣ ምጽዋትን መስጠት›› ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 8 / ሙስሊም 16)