የንግድ ግንኙነትህ

ኢስላም፣ አንድ ግለሰብ ሃብታምም ቢሆን ድሃ፣ ንብረቱን፣ ገንዘቡንና ሞያዊ መብቱን የሚያስከብሩና የሚያስጠብቁ ሕግጋትና ሥርዓቶችን አስቀምጧል፡፡ እንዲሁም ማኅበረሰቡ እርሱ በርሱ በሚተሳሰርበትን፣ ተደጋግፎ የሚያድግበትንና የሚበለጽግበትን የሕይወት ዘርፍን በማመቻቸትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡