ንፅህናህ

አላህ (ሱ.ወ) አንድ ሙስሊም ውስጣዊ አካሉን-ልቦናውን ከማጋራትና እንደ ምቀኝነት፣ ኩራትና ተንኮል ካሉ የልብ በሽታዎች፣ውጫዊ አካሉን ደግሞ ከነጃሳና ቆሻሻ ከሆኑ ነገሮች እንዲያፀዳ አዟል፡፡ ይህን ከፈፀመ የአላህን ውዴታ ይጎናጸፋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡-«አላህ (ከኀጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፡፡ ተጥራሪዎችንም ይወዳል፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 222)